ሰሙኝማ ወዳጆቼ አሁን ይህቺን ቁርጥራጭሬ ልሞነጫጭር የተነሳሁት በመከራ ያመጣሁት ዕንቅልፌ ሊወስደኝ ጫፍ ላይ ከደረሰ በኋላ ተነስቼ ነው፡፡አሁን ሰዓቱ ከለሊቱ 6፡48 ደቂቃ
ነዉ፡የመሞነጫጨር አባዜ ኖሮብኝ አይደለም በዚህ ውድቅት ለሊት ከሞቀ መኝታዬ በመነሳት መብራት አብርቼ ጠረጴዛዬ ላይ የተሰየምኩት፡፡በገዛ ቤቴ፥መኝታዬ ላይ አትተኛም ተብዬ ነው መነሳቴ፡፡
እኔ የምለው እነኚህ የእምነት ተቋማት የሚገዟቸውን የድምፅ ማስጮሂያ መሳሪያዎች ከህንፃው ዉጭ የሚሰቅሏቸው ለምንድነው?ለምንስ በዚያ ስፍራ የሚካሄደውን የአምልኮ ወይም የትምህርት ስነ ስርዓት ፈልጎ በስፍራው ለተገኘው ምዕመን ብቻ ድምፁን መጥነው አይጠቀሙበትም?ይሄ በጣም የሚያሳዝነኝ እና የሚያስገርመኝ አይነኬ የሆነ የብዙዎቹ ቤተ ዕምነቶች የተለመደ የዘወትር ተግባራቸው ነው፡፡በእኔ ዕምነትነና ትዝብት መሰረት የትኛዉም የእምንት ተቋም ከዚህ ተግባር የፀዳ አይደለም፡፡አሁን እስቲ ትምህርቱን ፈልጎ በስፍራው የተገኘው ምዕመን እያለ ቤቱ የተኛው የዕምነቱ ተከታይ የሆነ ወይም ያለፀሆነዉ ሰው ለምን ይረበሻል?አሁን እኔንም የረበሸኝ በአካባቢዬ ያለ አንድ የቤተ እምነት ድምፅ ነው፡፡የቀኑንስ እሺ ይሁን ለምደነዋል፡አሁን በዚህ ውድቅት ለሊት በገዛ ቤቱ በሞቀ እንቅልፍ ላይ ያለ ሰው ለምን ይረበሻል?ያለ ዲምፅ መሳሪያስ ቢመለክ?እግዚአብሔር አይሰማ ይሆን?እባካችሁ ቢያንስ እስኪነጋ እንኳን የውጪውን መስመር አጥፉት?እኔም በመከራ የመጣ እንቅልፌን ለመመለስ አንድ 30 ደቂቃ ልገላበጥ፡፡
ሐምሌ 30/2003 ዓ.ም
No comments:
Post a Comment