እንደገና የተሰኘዉን የኢቲቪ ዘጋቢ ፊልም ስመለከት አንድ ወጣት የላሊበላ ዉቅር አብያተ ክርስትያናት በር ላይ ቆሞ በኢትዮጵያዊነቴ እኮራለሁ ሲል ሰማሁትና ዉስጤ ዝብርቅረቅ ያለ ስሜት ወረረኝ፡፡አሁን ላሊበላ፣አክሱም፣የፋሲል ቤተ መንግስት፣የሀረር ግንብን የሰሩ ዜጎች የኖሩባት ሀገር ዜጋ መሆን ምኑ ነዉ የሚያኮራዉ?አሁን አስቲ አባቴ ጀግና ነበር ብሎ ማዉራት ጉራ ከመንፋት ያለፈ ምን ፋይዳ አለዉ?የነሱ ልጅ ነኝ ስለሆንኩም ደግሞ እኮራለሁ ምን ይባላል?አሁን የዛን ዘመን ሰዎች ታሪክ እያወሩ በትዝታ መኖር ምን ለመፍጠር ነው? ባይሆን የኛ ታሪክ የወሎ ረሀብ፣ለ 30 ዓመታት የዘለቀዉ የእርስበርስ ፍጅት፣ወዘተ…ነዉ፡፡ምክንያቱም በዚህ ዘመን ስለኖርን በሱ ብናፍርም ወይም ደግሞ ብንኩራራም ያምርብናል።ለነገሩ እነኚህን ድንቅ ቅርሶች ትተዉልን ያለፉት ሰዎች በርግጥ ኢተዮጵያውያን ናቸዉን?እኔ ግን የሚመስለኝ ወይ ሰዎቹ ሰረተዉ ከሄዱ በኋላ ነዉ እኛን መሳዮቹ የኛ ወላጆች ወደዚህ አካባቢ የመጡት አሊያም የኛ ሰዎች ጥበብ አምሯቸዉ ከሌላ ፕላኔት አሊያም ከሆነ ቦታ አነዚህን የጥበብ ሰዎች አስመጥተዋቸዉ ይሆናል፡፡ለነገሩ ፕ/ር አነድሪያሰ ባሉት በጣም እስማማለሁ “ታሪካችኝ ይበዛብናል” ነበር ያሉት?እውነት አይመስላችሁም? ለዚህም ይመስለኛል ከማንነታችን በላይ የገዘፈ ታሪክ እያወራን፡እነእንቶኔን እኮ ድሮ እንበልጠቸዉ ነበር ቅብርጥሴ እያልን የቀረነዉ።አሁን ደግሞ አዲሷ አገር ደቡብ ሱዳን ነገ ስትበልጠን እንደለመደብን ድሮ እንበልጣት ነበር እንል ይሆን?መቼ ይሆን በሞቱ ሰዎች ታሪክ መኩራራቱን ትተን እኛ በሰራነዉና በምንሰራዉ ማፈር የምንጀምረዉ?ይሄን የምለዉ ያለንበትን ማወቁ ለለዉጥ ጅማሬዉ ነው ብዬ ነዉ፡እንደዚያ ብናደርግ ታሪካቸውን ለ ዉጭ ሀገር ሰው እያሳየን የምንኮራባቸዉ የዚያ ዘመን ሰዎች አፅምም በእፎይታ የሚያርፍ ይመስለኛል።
No comments:
Post a Comment